Sufian Ahmed among candidates for AfDB chief - DireTube News

1,373 views · Published 21 February 2015 · 1:32 · Indexed 20 September 2026

Channel: News ET Social · 2015 · Entertainment

Watch on YouTube

Sufian Ahmed among candidates for AfDB chief ... Read More at ... http://goo.gl/ultvoE | የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ሚንስትር አቶ ሱፊያን አሕመድ የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንትን ለመተካት እጩ ሆነው ቀርበዋል…

የብሉምበርግ ዘገባ እንደሚያስረዳው፣ የአፍሪካ ልማት ባንክን በፕሬዝዳንትነት ለመምራት እጩ ሆነው ከቀረቡት ስምንት ግለሰቦች መካከል ሶስት የአፍሪካ የፋይናንስ ሚንስትሮች ይገኙበታል ተብሏል - ከነዚህም ውስጥ አንዱ የኢትዮጵያ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ሚንስትር የሆኑት አቶ ሱፊያን አሕመድ አንዱ ናቸው፡፡

የቻድ የፋይናንስ ሚንስትር የሆኑት ኮርጄ ቤዱምራ እንዲሁም የኬፕ ቨርዴው ክሪስቲና ዱዋርቴም እጩ ሆነው ቀርበዋል፡፡

የአፍሪካ ልማት ባንክን ላለፉት 10 ዓመታት በፕሬዝዳንትነት የመሩት ዶናልድ ካበሩካ የአመራር ዘመናቸው በመጪው ነሐሴ ወር ይገባደዳል ተብሏል፡፡

የአፍሪካ ልማት ባንክ ቦርድ አዲሱን የባንኩን ፕሬዝዳንት እ.አ.አ በግንቦት 28 2015 በአይቮሪ ኮስቷ አቢጃን በሚካሄድ ስብሰባ ላይ ይመርጣል ተብሏል፡፡

ዝርዝሩን ይመልከቱ…

-~-~~-~~~-~~-~-
Please watch: "Kaleab Mulugeta - Enja Semonun (እንጃ ሰሞኑን) ❤ New! Ethiopian Music Video 2017" 
https://www.youtube.com/watch?v=AZ1yRHGb4bY
-~-~~-~~~-~~-~-

More from this channel