America's Allies Are Funding ISIS - DireTube News

3,153 views · Published 9 May 2015 · 1:37 · Indexed 12 November 2026

Channel: News ET Social · 2015 · Entertainment

Watch on YouTube

America's Allies Are Funding ISIS | Read More at...http://goo.gl/m1beOh | አሜሪካና ባልንጀሮቿ አይኤስን በመደገፍ ተወነጀሉ

ሳውዲ አረቢያ፣ ኩዌትና ኳታር እጅግ ጥብቅ የሚባሉ የአመሬካ ባልንጀሮች የባህረሰላጤው ሀገራት ናቸው፡፡ ሀገራቱ ከአሜሪካ ጎን በመቆም ጽንፈኝነትን እንደሚዋጉ ሲምሉና ሲገዘቱ ቆይተዋል የሚለው የዴይሊ ቢስት ዘገባ ይሁን እንጂ እነኚሁ ሀገራት እንደ አይኤስአይኤስ ያሉ አለምን ያሸበሩ ጽንፈኛ ሀይሎችን በገንዘብና በሌላም ሲደግፉ መቆየታቸውን ነው የዘገበው፡፡

እነኚህ የባህረሰላጤው ሀገራት እጅግ በጠላትነት የሚፈርጇትን ኢራንን እንዲሁም የኢራን ወዳጅ የሆነውን የሶሪያውን የአላሳድ መንግስትንና የሺአ እስልምና ተጽእኖን በአካባቢው ለመመከት ሲሉ በሶሪያና በኢራቅ ድንበሮች ዋነኛ መመሸጊያውን ያደረገውን አይኤስአይኤስ የሽብር ቡድንን ጡንቻ ሲያፈረጥሙ መኖራቸው ነው በዘገባው የተነገረው፡፡

እስላማዊ መንግስት ነኝ የሚለው አይኤስ የሽብር ቡድን እንዲፋፋና ዛሬ ለደረሰበት አለምን የማተራመስ እንቅስቃሴ እንዲበቃ የለዘብተኛ ሱኒ እስልምና እምነትን እንከተላለን የሚሉት በነዳጅ የናጠጡት የሼኮች ሀገራት ከጭቃ ሹማቸው አሜሪካ ጋር እየተመሳጠሩ ለጽንፈኛው ቡድን የንጹሀን ማረጃ ቢላና ጠመንጃ ሲያቀብሉት እንዴት እንደኖሩ ይሄው ዴይሊ ቢስት በዘገባው በሰፊው ያብራራል፡፡

ሀገራቱ አሁን ላይ ለይስሙላ ጽንፈኝነትን እንከላከላለን ይበሉ እንጂ በሰው ልጆች ታሪክ ታይቶ የማያውቅ ጭካኔ የሚፈጽም አረመኔያዊ የሽብር ቡድንን ከማስፈልፈል በስተጀርባ ተጠያቂነት እንዳለባቸው ነው ዘገባው ያተተው፡፡

-~-~~-~~~-~~-~-
Please watch: "Kaleab Mulugeta - Enja Semonun (እንጃ ሰሞኑን) ❤ New! Ethiopian Music Video 2017" 
https://www.youtube.com/watch?v=AZ1yRHGb4bY
-~-~~-~~~-~~-~-

More from this channel